BBC News, አማርኛ - ዜና
BBC News Amharic Top Stories
አላማጣ እና ኮረም ከተሞች እንዴት እየሰነበቱ ነው?
የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነትን ተከትሎ በአማራ ክልል ስር ሲተዳደሩ የቆዩት የራያ አካባቢዎች ያለ አስተዳዳሪ ወደ ሁለተኛ ሳምንታቸው እየተሻገሩ ነው። ከየካቲት ጀምሮ አልፎ አልፎ ሲከሰት የነበረው “በህወሓት ታጣቂዎች” እና “በአካባቢው ሚሊሺያዎች” መካከል ሲደረግ የነበረው የተኩስ ልውውጥ ከሚያዝያ 5/2016 ዓ.ም. ጀምሮ ከፍ ባለ ሁኔታ ተካሂዶ ከሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ወዲህ የነበረውን መዋቅር ቀይሮታል።
በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ እንዳሳሰባቸው የአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበር ገለጹ
በአማራ እና በትግራይ ክልሎች መካከል የይገባኛል ውዝግብ ባለባቸው አካባቢዎች ላይ እየታየ ያለው ሁኔታ በእጅጉ እንዳሳሰባቸው የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማሐማት ገለጹ። ሊቀመንበሩ ባወጡት መግለጫ በሰሜን ኢትዮጵያ ራያ አላማጣ፣ ዛታ እና ኦፍላን ጨምሮ አወዛጋቢ በሆኑት አካባቢዎች ባሉ ማኅበረሰቦች መካከል “እየተባባሰ ያለውን ውጥረት” ስጋት ውስጥ ሆነው እየተከታተሉት መሆናቸውን አመልክተዋል።
አርሰናል የሰሜን ለንደን ደርቢን ያሸንፋል? ወይስ የመርሲሳይድ ደርቢ ዕጣ ይደርሰዋል?
ሊቨርፑል በመርሲሳይድ ደርቢ በኤቨርተን መሸነፉ በዋንጫ ፉክክሩ ላይ ያለውን ተስፋ ሲያጨልምበት፤ አርሰናል በሜዳው ቼልሲን፤ ማንቸስተር ሲቲ ደግሞ ከሜዳው ውጪ ብራይተንን አሳማኝ በሆነ ውጤት አሸንፈዋል። በዚህ ሳምንት የሚደረጉ ጨዋታዎች የዘንድሮውን ዋንጫ ወደ የትኛው ክለብ ሊያመራ እንደሚችል ሊጠቁመን ይችላል። ሊቨርፑል በአውሮፓ መድረክ የመጫወት ተስፋ ካለው ዌስት ሃም ጋር ከሜዳው ውጪ ይጋጠማል። አርሰናል በሰሜን ለንደን ደርቢ በቶተነሃም ሜዳ ይፈተናል። ሲቲ ደግሞ ከወራጅ ቀጠና ለመውጣት ወደ ሚታገለው ፎረስት ያቀናል። የቢቢሲው የእግር ኳስ ተንታኝ ክሪስ ሱተን የፕሪሚየር ሊግ ግምቶቹን እንደሚከተለው ሰጥቷል።
ቻይና ‘ቀይ መስመር’ ያለችውን እንዳታልፍ አሜሪካን አስጠነቀቀች
የቻይን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋሽንግተን የአገራቸውን “ቀይ መስመር” እንዳታልፍ ለአሜሪካው አቻቸው አስጠነቀቁ።
ዐቃቤ ሕግ በቀድሞው የሰላም ሚኒስቴር ዲኤታ አቶ ታዬ ደንደአ ላይ ሦስት ተደራራቢ ክሶችን መሠረተ
“መንግሥትን ለመጣል ሲያሴሩ ነበር” በሚል በቁጥጥር ስር የዋሉት የድሞው የሰላም ሚኒስቴር ዲኤታ አቶ ታዬ ደንደአ በዐቃቤ ሕግ ሦስት ተደራራቢ ክሶች እንደተመሠረተባቸው ጠበቃቸው ለቢቢሲ ተናገሩ።
በኢትዮጵያ አየር መንገድ አደጋ ሕይወታቸውን ያጡ መንገደኞች ቤተሰቦች ቦይንግ በወንጀል እንዲከሰስ ጠየቁ
በኢትዮጵያ አየር መንገድ 737 ማክስ 9 አውሮፕላን ከአምስት ዓመት በፊት ሕይወታቸውን ያጡ መንገደኞች ቤተሰቦች ለአደጋው መንስዔ የሆነው የአውሮፕላን አምራቹ ቦይንግ ላይ የወንጀል ክስ እንዲመሠረት የአሜሪካ የፍትህ መሥሪያ ቤትን ጠየቁ።
በእስራኤል ጥቃት ከተገደለች እናት ማህጸን በሕይወት ወጥታ የነበረችው ጨቅላ አረፈች
እስራኤል በደቡባዊ ጋዛ በፈጸመችው ጥቃት ከተገደለች ፍልስጤማዊት እናት ማህጸን በሕይወት መውጣት ችላ የነበረችው ጨቅላ ከቀናት በኋላ አረፈች።
በትናንሽ ጀልባዎች ወደ ዩናይትድ ኪንግደም ምን ያህል ስደተኞች ይገባሉ? ከየትኞቹ አገራት የመጡ ናቸው?
ዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) በትናንሽ ጀልባዎች አቋርጠው ወደ ግዛቷ የሚገቡ ስደተኞች ቁጥር መጨመር በእጅጉ ስላሳሰባት አዲስ ሕግ አዘጋጅታ ከአገሯ በማስወጣት ወደ ሩዋንዳ ለመውሰድ አቅዳለች። ከፈረንሳይ ተነስተው ባሕር በማቋረጥ ወደ ዩኬ ምን ያህል ስደተኞች ይገባሉ? የየትስ አገራት ዜጎች ናቸው?
ምዕራባውያን ቢሊዮኖችን እያፈሰሱ ዩክሬንን የሚያስታጥቋት ዘመናዊ የጦር መሣሪያዎች
አሜሪካ ዩክሬንን የጦር መሣሪያ ለማስታጠቅ ከ60 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ በዚህ ሳምንት አጽድቃለች። በሩሲያ የተከፈተባትን ወረራ ተከትሎ ጦርነት ውስጥ ለምትገኘው ዘመናዊ መሣሪያዎችን ለማቅረብ ምዕራባውያን ቢሊዮን ዶላሮችን እያፈሰሱ ነው። ለዩክሬን ምን ዓይነት የጦር መሣሪያዎች ናቸው የሚቀርቡት?
ታንዛንያን ያጥለቀለቃት ጎርፍ ከ150 ሰዎች በላይ ህይወት ቀጠፈ
በታንዛንያ ከባድ ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ እና የመሬት መንሸራተት የ155 ሰዎች ህይወት መቀጠፉን የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አስታወቁ።
የጋዛን ጦርነት በሚቃወሙ እንቅስቃሴዎች ምክንያት ታዋቂው የአሜሪካ ዩኒቨርሲቲ የምረቃ ፕሮግራም ተሰረዘ
በሎሳንጀለስ የሚገኘው የደቡብ ካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ በመጪው ግንቦት 2/2016 ዓ.ም ሊያደረገው የነበረው ዋና የምረቃ ፕሮግራም ከደህንነት ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ተሰርዟል። በሎስ አንጀለስ የሚገኘው የደቡብ ካሊፎርኒያ ዩኒቨርስቲ በመጪው ግንቦት 2/2016 ዓ.ም ሊያደርገው የነበረው ዋና የምረቃ ፕሮግራም ከደህንነት ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ተሰርዟል።
በናይጄሪያ በከባድ ዝናብ ምክንያት ጉዳት ከደረሰበት ማረሚያ ቤት ከ100 በላይ እስረኞች አመለጡ
በናይጄሪያ የጣለው ከባድ ዝናብ በአንድ ማረሚያ ቤት ክፍሎች እና በአጥሩ ላይ ጉዳት በማድረሱ ከ100 በላይ እስረኞች አመለጡ።
አነጋጋሪ ጉዳይ
ቀሲስ በላይ መኮንን፤ በሐሰተኛ ሰነድ ገንዘብ ለማውጣት በተሞከረበት ቦታ የተገኙት “ሰዎች አታለዋቸው” መሆኑን ተናገሩ
ሐሰተኛ ሰነድ በመጠቀም ከስድስት ሚሊዮን ዶላር በላይ ለማውጣት በመሞከር የተጠረጠሩት ቀሲስ በላይ መኮንን፤ ድርጊቱ በተፈጸመበት ቦታ የተገኙት “ሰዎች አታልለዋቸው” እንደሆነ ለፍርድ ቤት መግለጻቸውን ጠበቃቸው አቶ ቱሊ ባይሳ ለቢቢሲ ተናገሩ።
ጣልያን ለኢትዮጵያውያን ስደተኞች ምን ያህል ምቹ ናት?
በዕድሉ መንገሻ እና አበባ ተስፋዬ በተለያየ ጊዜ ከሱዳን ተነስተው፣ የሊቢያ በርሃን አቆራርጠው፣ የሜድትራኒያንን ባህር ሰንጥቀው ነበር ጣልያን የደረሱት። በዚያ ጉዞ የሰው ልጅ ሊሸከመው የማይችለው ፈተናን አይተዋል። ጭው ባለ በርሃ የሰው ልጆችን የሰውነት ቅሪት እየተመለከቱ፣ እየተደበደቡ፣ እየተራቡ፣ እየተጠሙ እና በህይወታቸው ‘እየቆመሩ’ የተመኟትን ጣልያን ከረገጡ ዓመታትን አስቆጥረዋል። ተስፋ ያደረጓት ጣልያን እንዴት ተቀበለቻቸው? ጣልያን ለኢትዮጵያን ስደተኞች ምን ያህል ምቹ ናት? የቢቢሲ ጋዜጠኞች ጣልያን በሄዱበት ወቅት ታሪካቸውን አጋርተዋል።
አቶ ጌታቸው ረዳ ከብልፅግና ጋር ስለመዋሃድ፣ ስለሰሞኑ ግጭት እና ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ስላላቸው ግንኙነት ምን አሉ?
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ ህወሓትን ከብልፅግና ፓርቲ ጋር ስለማዋሃድ፣ ስለሰሞኑ ግጭት፣ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ስላለቸው ግንኙነት እና የይገባኛል ጥያቄ ስለሚነሱባቸው አካባቢዎች ለቢቢሲ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
የመንገዶች አስተዳደር በተቋረጡ እና በቆሙ የመንገድ ፕሮጀክቶች ላይ የ35 ቢሊዮን ብር ካሳ በተቋራጮች ተጠየቀ
የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር “በፀጥታ ችግር” ምክንያት በተቋረጡ እና በቆሙ የመንገዶች ፕሮጀክቶች ላይ 34.95 ቢሊዮን ብር ካሳ በተቋራጮች መጠየቁን አስታወቀ። አስተዳደሩ እስከ 2016 በጀት ዓመት ስድስት ወራት ድረስ “በፀጥታ ችግር” ምክንያት “ሙሉ በሙሉ የኮንትራት ውላቸው የተቋረጠ” 31 የመንገድ ፕሮጀክቶች መኖራቸውንም ይፋ አድርጓል።
ስለ ክትባት ያልተረጋገጡ የሴራ ትንተናዎችን የሚያሠራጩት ተጽእኖ ፈጣሪ ፓስተር
“ክራይስት ኤምባሲ” የተባለው ቤተክርስቲያን መሥራች እና መሪ የሆኑት ናይጄሪያዊው ፓስተር ክሪስ ኦያኪሂሎሜ በስብከታቸው ውስጥ የሚያስተላልፉት መልዕክት ላይ ክስ ይቀርብባቸዋል። በተለይ በክትባት ዙሪያ የሚያሠራጩት የሴራ ትንተና በተለያዩ የአፍሪካ አገራት የሚገኙ ተከታዮቻቸውን ጤና አደጋ ላይ የሚጥል ነው እየተባለ ነው። ፓስተሩ ምን አሉ?
አንዳንድ አገራት ፍልስጤምን እንደ አገር ዕውቅና የማይሰጧት ለምንድነው?
ባለፈው ሳምንት የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ፍልስጤም የድርጅቱ ሙሉ አባል ለመሆን ባቀረበችው ጥያቄ ላይ ድምፅ ሰጥቷል። ዩናይትድ ስቴትስ ድምፅን በድምፅ የመሻር ሥልጣኗን ተጠቅማ ይህን ጥያቄ ውድቅ ብታደርገውም 12 የምክር ቤቱ አባላት ድጋፋቸውን ሰጥተዋል። ነገር ግን የአገርነት ጥያቄዋ ተቀባይነት አላገኘም። አንዳንድ አገራት ለፍልስጤም የአገርነት ዕውቅና ለምን ይነፍጓታል?
ከሶማሊያ ጋር ወታደራዊ ስምምነት የደረሰችው የቱርክ የጦር መርከብ ሞቃዲሾ ወደብ ደረሰች
ከጥቂት ወራት በፊት በሶማሊያ እና በቱርክ መካከል የተደረሰውን የወታደራዊ ትብብር ስምምነትን ተከትሎ የቱርክ ባሕር ኃይል የጦር መርከብ ሞቃዲሾ ወደብ ደረሰች።
በሁለት ሳምንት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ በደረሰ የጀልባ አደጋ 21 ስደተኛ ኢትዮጵያውያን ሞቱ
በሁለት ሳምንት ልዩነት ውስጥ ዳግም ቀይ ባሕር ላይ ባጋጠመ የጀልባ መስመጥ አደጋ የ21 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ሕይወት ማለፉ ተገለጸ።
በደቡብ ጎንደር አምስት ሰዎች ሲገደሉ 18 ቤቶች መቃጠላቸውን ተጎጂዎች እና የዐይን እማኞች ተናገሩ
በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ዞን እስቴ ወረዳ አጎና በተባለ ‘የቀበሌ ከተማ’ ባለፈው ሰኞ ሚያዚያ 7/2016 ዓ.ም. በፋኖ እና በመንግሥት ኃይሎች መካከል የተካሄደ ግጭትን ተከትሎ ነዋሪዎች መገደላቸውን እና በርካታ ቤቶች መቃጠላቸውን የተጎጂ ቤተሰቦች እና የዐይን እማኞች ለቢቢሲ ተናገሩ።
ዩኬ ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ የምትልክበት ሕግ ምንድን ነው? ተፈጻሚነቱስ በማን ላይ ነው?
ለበርካታ ወራት ብዙ ሲያወዛግብ የቆየው ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ የሚልከው ሕግ በዩናይትድ ኪንግደም ፓርላማ ጸድቆ ሕግ ሆኗል። ይህ ሕግ ምን አካቷል? የትኞቹንስ ስደተኞች ይመለከታል?
ዩክሬን እና ሩሲያ ሱዳን ውስጥ በእጅ አዙር ጦርነት እያካሄዱ ነው?
መስከረም 2016 ዓ.ም. ላይ በማይገመት ቦታ፣ ጨርሶ ሊገመቱ በማይችሉ ሁለት መሪዎች መካከል ስብሰባ ተደረገ። የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቭሎድሚር ዜሌንስኪ ከሱዳኑ መሪ ጄኔራል አብደል ፋታህ አል-ቡርሃን ጋር በአየርላንድ በሚገኝ አየር ማረፊያ መገናኘታቸው ብዙዎችን አስደንቆ ነበር።
የኢትዮጵያውያን ስደተኞች መዳረሻ የሆነችው ደቡብ አፍሪካ ያቀደችው የኢሚግሬሽን ማሻሻያ ምን ይዟል?
የበርካታ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች መዳረሻ የሆነቸው ደቡብ አፍሪካ እየሠራችበት ያለውን ‘የቅኝ ግዛት’ የኢሚግሬሽን ሥርዓት ልታሻሽል መሆኑን አስታውቃለች። የደቡብ አፍሪካ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር የአገሪቱ የኢሚግሬሽን ሕግጋት ጠበቅ ያሉ እንዲሆኑ እና የዜግነት እንዲሁም የጥገኝነት ሂደቶችን የሚያሻሽለውን አዲሱን ዕቅድ ይፋ አድርገዋል።
ከየፈርጁ
የብልፅግና ፓርቲ ‘የሚዲያ ሠራዊት’ አባላት በሐሰተኛ መረጃ ሥርጭት እና አሳሳች የፌስቡክ ዘመቻዎች ላይ መሳተፋቸውን የቢቢሲ ምርመራ አረጋገጠ
በገዢው ብልፅግና ፓርቲ በተለይም በአዲስ አበባ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ስር የሚንቀሳቀሱ እና ‘የሚዲያ ሠራዊት’ የሚል መጠሪያ ያላቸው የፓርቲው አባላት፤ መንግሥትን በሚተቹ እና በሚቃወሙ ግለሰቦች ላይ በፌስቡክ በተደረጉ የሐሰተኛ መረጃ እና በተቀናጁ ዘመቻዎች ላይ እንደተሳተፉ ቢቢሲ ያደረገው ምርመራ አረጋገጠ።
የውጭ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ ከወጪ እስከ ችርቻሮ ንግድ ዘርፍ መግባታቸው በረከት ወይስ ስጋት?
ኢትዮጵያ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ለውጭ ባለሃብቶች ዝግ ሆነው የኖሩ የምጣኔ ሃበት ዘርፎችን እየከፈተች ነው። በቅርቡ ድግሞ ለኢትዮጵያውያን ብቻ ተጠብቀው የነበሩት የወጪ፣ የገቢ፣ የጅምላ እና የችርቻሮ ንግድ ዘርፎች ክፍት እንዲሆኑ ተወስኗል። ይህ ውሳኔ የአገር ውስጥ ባላሃብቶችን እና ነጋዴዎችን ከገበያ ያስወጣል የሚሉ እንዳሉ ሁሉ፤ ውድድርን በመፍጠር ለሸማቾች አማራጮችን ያቀርባል የሚሉ አሉ። የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች ምን ይላሉ?
ትውልደ ኢትዮጵያውያኑ የተሳተፉበት የነፍስ አድን ጥረት በአሜሪካ
አሜሪካ ውስጥ በድንገት በደረሰ አደጋ ምክንያት ከመንገድ ወጥቶ በእሳት በተያያዘ መኪና ውስጥ የነበረ ግለሰብን ሕይወት ያተረፉ ሁለት ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና ሌሎችም አድናቆት እየተቸራቸው ነው። መኪና ላይ በተገጠመ ካሜራ የተቀረጸው ቪዲዮ እንደሚያሳየው ትውልደ ኢትዮጵያዊያኑ እና ሌሎችም በመንገዱ ላይ ሲያልፉ የነበሩ ሰዎች በእሳት ከተያያዘው መኪና አንድን ግለሰብ ለመታደርግ ያደረጉትን አስደናቂ ጥረት አሳይቷል።
በአዲስ አበባ የግንባታ ድንጋይ እና አፈር ተደርምሶ የ4 ዓመት ህጻንን ጨምሮ የ7 ሰዎች ሕይወት አለፈ
በአዲስ አበባ ከተማ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ልዩ ስሙ ጠሮ መስጂድ በተባለ አካባቢ ለቤት ግንባታ የተከመረ ድንጋይ እና አፈር ተንዶ የሰባት ሠዎች ሕይወት አለፈ።
እስራኤል እና ኢራን ጦርነት ውስጥ ቢገቡ ምን ይከሰታል? በወታደራዊ አቅምስ ይመጣጠናሉ?
ኢራን እና እስራኤል እስካለፈው ሳምንት ድረስ በእጅ አዙር እንጂ በቀጥታ ግጭት ውስጥ ገብተው አየውቁም። አሁን ግን በሚሳኤል እና በድሮኖች አንደኛው በሌላኛው ላይ ግልጽ ጥቃት መፈጸም ጀምረዋል። ለመሆኑ እስራኤል እና ኢራን ጦርነት ውስጥ ቢገቡ ምን ሊከሰት ይችላል? ሁለቱ አገራትስ በወታደራዊ አቅም ምን ያህል ይመጣጠናሉ?
ኢትዮጵያ፡ 56 በመቶ የሚሆኑ የሁለተኛ እና ሦስተኛ ክፍል ተማሪዎች ፊደል መለየት እንደማይችሉ ጥናት አመለከተ
በኢትዮጵያ ከሚገኙ የሁለተኛ እና ሶስተኛ ክፍል ተማሪች 56 በመቶዎቹ ምንም ዓይነት ቃል ማንበብ እንደማይችሉ ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ባደረገው ጥናት አመልክቷል። አገልግሎቱ በጥናቱ ተሳተፊ ካደረጋቸው የሁለተኛ ክፍል ተማሪዎች መካከል ቢያንስ አንድ ቃል ማንበብ የሚችሉ 37 በመቶ የሚሆኑት ብቻ እንደሆኑ በአገልግሎቱ የትምህርት ምዘናና ምርምር መሪ ስራ አስፈጻሚ ኤፋ ጉርሙ (ዶ/ር) ለቢቢሲ ገልጸዋል። የተቀሩት 63 በመቶዎቹ አንድም ቃል ማንብብ የማይችሉ (Zero renderers) ናቸው።
ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ዘርፌ ወንድማገኝ ለአምስት ዓመታት ከአትሌቲክስ ታገደች
የ21 ዓመቷ የመካከለኛ ርቀት አትሌት ለአምስት ዓመታት መታገዷን የገለጠው አትሌቲክስ ኢንቴግሪቲ ዩኒት የተባለው ተቋም ነው። ተቋሙ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጹላ በለጠፈው መግለጫ አትሌቷ ምርመራ ከተደረገላት በኋላ ቅጣት ማስተላለፉን አሳውቋል።
ረሃብ ባንዣበበባት ሱዳን ከጦርነቱ ከሚሸሹ ሰዎች የሚሰሙ የግድያ እና የመደፈር ታሪኮች
አንድ ዓመት ያለፈው የሱዳን የእስር በርስ ጦርነት እንደቀጠለ ነው። በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን የገደለው ጦርነት ሚሊዮኖችን አፈናቅሏል። ፤ሎች ሚሊዮኖች ደግሞ በረሃብ አፋፍ ላይ ከሚገኙባት ሱዳን ዘግናኝ የግድያ እና ፆታዊ ጥቃት ታሪኮች እየተሰሙ ነው።
ኢራን እና እስራኤል ለምን ደመኛ ጠላቶች ሆኑ?
ኢራን ከግብፅ ቀጥላ ለእስራኤል እውቅና በመስጠት ሁለተኛዋ እስላመዊ አገር ነበረች። ነገር ግን ከኢራን እስላማዊ አብዮት በኋላ ይህ ግንኙነት ተበላሽቶ ከአምስት አስርታት በላይ በጠላትነት እየተያዩ ቆይተዋል። ለመሆኑ የሁለቱ አገራት ግንኙነት ወደ ደመኛ ጠላትነት ለምን ተሸጋገረ?
ቪዲዮ, አንድ ዓመት በሞላው ጦርነት ለውስብስብ ችግር የተጋለጡት ሱዳናውያን ክርስቲያኖችርዝመት, 1,54
ባለፈው ዓመት የተቀሰቀሰው የሱዳን ጦርነት ክርስቲያኖችን አጣብቂኝ ውስጥ ከቷቸዋል። በጦርነቱ መጀመሪያ አካባቢ ክርስቲያኖች በተለየ መልኩ ተጠቅተዋል የሚሉ መረጃዎች ሲወጡ ነበር። አብያተ ክርስቲያናት ተዘርፈዋል፤ አንዳንዶቹም በከባድ መሣሪያ ጥቃት ደርሶባቸዋል። ከአንድ ዓመት በኋላ ብዙዎቹ ወደ ግብፅ ሲሰደዱ፣ ቀሪዎቹም ተጠልለው ከሚገኙበት ፖርት ሱዳን ለመሰደድ አማራጮችን እየፈለጉ ነው።
ቪዲዮ, ምንጩ ከኢትዮጵያ የሆነው ቡና ለጤና እና ለዓለም ሥልጣኔ ስላበረከተው አስተዋጽኦ በጥቂቱርዝመት, 6,19
በዓለም ላይ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በየዕለቱ ቡና ይጠጣሉ። ቡና ቢያንስ ላለፉት 1500 ዓመታት እንደተጠጣ ይነገራል። ምንጩ ከኢትዮጵያ የሆነው ይህ ፍሬ ዛሬ ዓለም ላለችበት ዕድገትም የራሱን አስተዋጽኦ አድርጓል በማለት ምሁራን ይጠቅሱታል። በሌላ በኩል በሰውነታችን ውስጥ የተለያዩ በሽታዎችን በመከላከልና አዕምሮን በማንቃት አስተዋጽኦ እንዳለው የጤና ሙያተኞች ይመሰክራሉ። ቢቢሲ በዚህ ቪዲዮ ስለቡና ታሪካዊ ዳራ፣ ጠቀሜታዎች እና የጎንዮሽ ጉዳቶች በአጭሩ አቅርቧል።
አጃኢብ!
በዓለም ላይ ግዙፍ ገደሎች የመኖርያ መንደሮችን እየዋጡ ነው
የአየር ንብረት ለውጥ ለሸለቆዎች መሸርሸር ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች ከፍተኛ የዝናብ መጠን እንዲኖር በማድረግ አሉታዊ ተጽዕኖ ይኖረዋል።
የኢራን መንግሥትን የተቃወመው ራፐር ሞት እንደተፈረደበት ጠበቃው ተናገረ
መንግሥትን የሚቃወሙ እንቅስቃሴዎችን በመደገፍ የታሰረው ኢራናዊ ራፐር በሞት እንዲቀጣ በፍርድ ቤት ውሳኔ መተላለፉን ጠበቃው ገለጸ።
ታዋቂው ደራሲ ሳልማን ሩሽዲ በስለት ተወግተው ዐይናቸውን ያጡባትን ዕለት ሲያስታውሱ
ታዋቂው ደራሲ ሰር ሳልማን ሩሽዲ ከሦስት አስርት ዓመታት በፊት ባሳተሙት መጽሐፋቸው ምክንያት ተደጋጋሚ የግድያ ዛቻ ሲሰነዘርባቸው ቆይተው ከሁለት ዓመት በፊት ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል። በዚህም አንድ ዐይናቸውን ያጡ ሲሆን፣ ያቺን ዕለት ሲያስታውሱ የዐይን ብርሃናቸውን ማጣታቸው ማጣታቸው በእጅጉ እንደሚያንገበግባቸው ይናገራሉ።
በቦኮሃራም የታገተችው ናይጄሪያዊት ተማሪ ከ10 ዓመት በኋላ ሦስት ልጆችን ወልዳ ነጻ ወጣች
ከአስር ዓመት በፊት በቦኮሃራም ታጣቂዎች ታግተው ከነበሩ ሴቶች መካከል አንዷ የሦስት ልጆች እናት ሆና በናይጄሪያ መንግሥት ወታደሮች ነጻ ወጣች።
አደገኛ በመሆኑ ከገበያ እንዲሰበሰብ ስለተባለው የህጻናት የሳል ሽሮፕ ምን እናውቃለን?
ቢያንስ አምስት የሚሆኑ የአፍሪካ አገራት የተወሰኑ የጆንሰን ኤንድ ጀንሰን የሳል ሽሮፖች ከገበያ እንዲሰበሰቡ አዘዋል። “እጅግ ከፍተኛ” መርዛማ እና የመግደል አቅም ያለው ዳይትሊን ግላይኮል የተባለውን ንጥረ ነገር በምርመራ እንዳገኙበት ገልጸዋል።
ቪዲዮ, በበርካታ አገራት ከተሞችን በማውደም አሳሳቢ አደጋን እየጋረጠ ያለው የመሬት መንሸራተትርዝመት, 3,44
በዚህ ዘመን የመሬት መንሸራተት በበርካታ የዓለም አካባቢዎች አሳሳቢ እየሆነ የመጣ ክስተት ነው። ባለሙያዎች እንደሚሉት ሁኔታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል። በደቡብ አሜሪካ እና በአፍሪካ የሚገኙ አንዳንድ ከተሞችም ለውድመት ሲዳረጉ፣ በርካታ ሰዎችም ሕይወታቸውን አጥተዋል። የመሬት መሸርሸር ተፈጥሯዊ ቢሆንም ሰው ሰራሽ ምክንያቶች እንዳባባሱት ባለሙያዎች ይገልጻሉ። በዚህም ሳቢያ በአፍሪካ እና በደቡብ አሜሪካ ያሉ ከተሞች አደጋ ተጋርጦባቸዋል።
በእስራኤል ጥቃት በአንድ ላይ ስለተገደሉት የሐማስ መሪ ልጆች እና የልጅ ልጆች ምን እናውቃለን?
የሐማስ የፖለቲካ መሪ እስማኤል ሃኒዬህ ሦስት ልጆች እና አራት የልጅ ልጆቻቸው ረቡዕ ዕለት እስራኤል ጋዛ ውስጥ በፈጸመችው የአየር ጥቃት ተገድለዋል። ለመሆኑ የተገደሉት የሃንዬህ ልጆች በሐማስ ወታደራዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ተሳትፎ አላቸው?
ቡና እንዴት በዓለማችን በብዙዎች የሚወደድ አነቃቂ ፍሬ ሊሆን ቻለ?
እንቅልፍ ከማትተኛው የኒው ዮርክ ከተማ እስከ ኢትዮጵያ ተራሮች ድረስ ዝናው የናኘ ነው፤ ቡና። ሚሊዮኖች ሳይጎነጩት መዋል አይቻላቸውም። ቡና ለ15 ክፍለ ዘመናት የሰው ልጆች ባህል ማዕከል ሆኖ ኖሯል። አንዳንዶች የ17ኛው እና የ18ኛው ክፍለ ዘመን አብርሆት ከቡና ነው የመነጨው ይላሉ።
ኢትዮጵያ ፆታዊ ጥቃት ፈጻሚዎችን ከሥራ እና ከማኅበራዊ ግልጋሎቶች የሚያገል ምዝገባ ልትጀምር ነው
የኢትዮጵያ መንግሥት ፆታዊ ጥቃት ፈጻሚዎችን የሚመዘግብ ሥርዓት ሊጀምር መሆኑን የሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ። ምዝገባው ፆታን መሠረት አድርገው የሚፈጸሙ ጥቃቶችን ለመከላከል እና ለመቀነስ ያለመ ነው የተባለ ሲሆን፣ በተለይ “ወሲባዊ ጥቃቶች ላይ ትኩረት” እንደሚያደርግ ተነግሯል።
100 ዓመት የደፈኑ የዕድሜ ባለፀጋዎች የሚጋሯቸው 8 ሥነ-ልቦናዊ ባህሪያት
አብዛኛዎቹ 100 ዓመት የደፈኑ የዕድሜ ባለፀጋዎች አሁንም ጤናማ ናቸው፤ ጥንካሬያቸው ያስቀናል፤ ከሰው ለማውራት ጉጉ ናቸው። በእንግሊዝኛው ሴንቴናሪያንስ ይባላሉ። 100 ዓመት ያለፋቸው የዕድሜ ባለፀጋዎች ናቸው። እነዚህ የዕድሜ ባለፀጎች የሚያመሳስሏቸው በርካታ የጋራ ባህሪያት አላቸው።
በተለያየ ዕድሜ ላይ የሚገኙ ልጆቻችንን ስለ አደጋዎች እንዴት ማስተማር እንችላለን?
ዕድሜ ሲጨምር ስለ አደጋ ያለ ግንዛቤም ያድጋል። ልጆች ግን ሊገጥማቸው የሚችለውን አደጋ ባለማወቅ በቀላሉ ለጉዳት ሊዳረጉ ይችላሉ። ታዲያ ልጆችን ስለ አደጋ እና ቅድመ ጥንቃቄ ማስተማር የሚቻለው እንዴት ነው? በተለያየ ዕድሜ ላይ ያሉ ልጆችን ስለ አደጋ ማስተማር የሚቻልባቸው መንገዶች አሉ።
ቪዲዮ, ቢቢሲ ያጋለጠው የአፍሪካውያን የቤት ሠራተኞች ሰቆቃ በባሕረ ሰላጤዋ አገርርዝመት, 5,25
በባሕረ ሰላጤው አገራት ሁለት ሚሊዮን የሚሆኑ የቤት ውስጥ ሠራተኞች ይገኛሉ። ኑሮን ለማቃናት ወደ አረብ አገራቱ ያቀኑት አፍሪካውያን ግን ሥራ እና ኑሮ ቀላል አልሆነላቸውም። አብዛኞቹ በአሠሪዎቻቸው ጉልበታቸው የሚበዘበዝ፣ አካላዊ እና ሥነ ልቦናዊ ጥቃት የሚፈጸምባቸው፣ በረሃብ የሚሰቃዩ እና ሌሎችም በደሎች ይደርስባቸዋል። ከእነዚህ መካከልም በተለይ ኦማን ውስጥ በሚገኙ አፍሪካውያን የቤት ሠራተኞች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት በተመለከተ ቢቢሲ የምርመራ ዘገባ ሠርቷል።
የተመለሱ ጥያቄዎች
በመላው ዓለም የሚከበረው የምድር ቀን ምንድን ነው? ምንስ ዓላማ አለው?
የምድር ቀን በመላው ዓለም ሚያዝያ 14/2016 ዓ.ም. (በአውሮፓውያኑ ሚያዝያ 22) በተለያዩ ዝግጅቶች በመላው ዓለም ይታሰባል። ይህ የምድር ቀን ምንድን ነው? ምንስ ዓላማ አለው?
የኢድ አል-ፈጥር በዓል ቀን የሚወሰነው እንዴት ነው?
1445ኛው የኢድ-አልፈጥር በዓል ዛሬ ረቡዕ ሚያዚያ 2/2016 በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት እየተከበረ ይገኛል። በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ ቅዱስ የሆነው የረመዳው ወር ሲጠናቀቅ ከፍ ያለ ሃይማኖታዊ ትርጉም የሚሰጠው የኢድ-አልፈጥር በዓል ይከበራል።
የአእምሮ ጤና እክል የሆነው ባይፖላር ዲስኦርደር ምንድን ነው? ለምንስ ከታዋቂው ሠዓሊ ጋር ተያያዘ?
በተቃራኒ የስሜት ጽንፎች ውስጥ መዋለል (ባይፖላር ዲስኦርደር) ከ100 ሰዎች ውስጥ በአንድ ሰው ላይ ይከሰታል። ስለዚህ የአእምሮ ጤና እክል ግንዛቤን ለማስፋት መጋቢት 21 በየዓመቱ የባይፖላር ዲስኦርደር ቀን ይታሰባል። ይህ ቀን ደግሞ የታዋቂው ሠዓሊ ቪንሰንት ቫን ጎ የልደት ቀን ነው። ዕለቱ ለምን ከእሱ ጋር ተያያዘ? ቫን ጎ ባይፖላር የአእምሮ ጤና ችግር ነበረበት?
የአሜሪካን ገመና ለዓለም ይፋ ያደረገው ጁሊያን አሳንጅ ማን ነው?
የአሜሪካን ገመና ለዓለም ይፋ ያደረገው ዊክሊክስ የተሰኘው ድረ ገጽ መሥራች ጁሊያን አሳንጅ ከሰሞኑ የበርካታ መገናኛ ብዙኃን ዋነኛ ርዕሰ ጉዳይ ሆኗል።
ችላ ተብለው በአሳሳቢ ደረጃ በመላው ዓለም እየተስፋፉ የመጡት የአባላዘር በሽታዎች
እንደ የዓለም የጤና ድርጅት መረጃ በመላው ዓለም በየቀኑ ከአንድ ሚሊዮን የሚበልጡ ሰዎች በግብረ ሥጋ ግንኙነት በሚተላለፉ በሽታዎች ይያዛሉ። ነገር ግን በትክክል በወሲብ የሚተላለፍ በሽታ ምንድን ነው? ዓይነቶቹ እና ምልክቶቹስ ምንድን ናቸው? ራሳችንን እንዴት መጠበቅ እንችላለን?
ማንኮራፋት እንዴት ትዳርን እስከ ማፍረስ ሊያደርስ ይችላል? ምንስ መፍትሄ አለው?
የማንኮራፍት መዘዙ እንቅልፍ ማሳጣት ብቻ አይደለም። ለሚያንኮራፋው እና ከጎን ለሚተኛ አካላዊ እና የአእምሮ ጤና ጉዳት ያስከትላል። ትዳር ሊያፈርስ ይችላል።
ፆም በሰውነታችን ውስጥ የሚያስከትለው ለውጥ እና የሚሰጠው ጥቅም ምንድን ነው?
ለእስልምና እና ለክርስትና እመነት ተከታዮች ዋነኞቹ የፆም ወቅት የሆኑት ረመዳን እና ዓቢይ ፆሞች ተጀምረዋል። የሁለቱም እምነቶነቶች ምዕመናን የፆሙን ጊዜ በየራሳቸው ሥርዓት እና ደንብ መሠረት የሚከውኑት ሲሆን፣ በየዕለቱ ለረጅም ሰዓታት ከምግብ እና ከውሃ ርቀው ይቆያሉ። በዚህ ጊዜ ታዲያ ፆም በሰውነት ላይ ምን ለውጥን ያስከትላል? ምንስ ጥቅም አለው?
በረመዳን የፆም ወቅት የትኞቹን ዓይነት ምግቦች መመገብ፣ የትኞቹንስ መተው አለብን?
ረመዳን የፆም ወቅት ሙስሊሞች በጉጉት የሚጠብቁት ጊዜ ነው። ከማለዳ ጀምሮ አስከ ምሽት ድረስ ምግብ ሳይቀመስ የሚቆይበት የፆም ጊዜ የመጀመሪያ ቀናት ለአንዳንዶች ፈታኝ ነው። በፆሙ ወቅት መደበኛ እንቅስቃሴያችንን እያደረግን ያለድካም ለመቆየት የሚያስችሉ ዘዴዎችን የሥነ ምግብ ባለሙያዎች ይመክራሉ። በዚህ ወቅት ምን ዓይነት ምግቦችን መመገብ፤ የትኞችንስ ማስቀረት አለብን?
ራስን ማጥፋት የሚያበረታታው እና ለበርካቶች ሞት ምክንያት የሆነው መርዝ ሻጭ በቢቢሲ ተጋለጠ
በዩናይትድ ኪንግደም ቢያንስ 130 ሰዎች ራሳቸውን አጥፍተውበታል የተባለውን መርዝ የሸጠውን ዩክሬናዊ ቢቢሲ ተከታትሎ ደርሶበታል። ሊዮኒድ ዛኩተንኮ የተባለው ይህ ግለሰብ ራስ ማጥፋትን የሚያበረታታበት እንዲሁም አገልግሎቱን የሚያስተዋውቅበት ድረ ገጽ አለው።
ማር ለጤናችን ምን ያህል ጠቃሚ ነው? መመገብ ያለባቸውስ እነማን ናቸው?
ከስኳር የሚጣፍጠው የተፈጥሮ ማር ብቸኛው የስኳር አማራጭ ነው? ለሁሉም ሰውስ በእኩል ይጠቅማል? ሕጻናትን ለመመገብስ የዕድሜ ገደብ አለው? የምንወስደው መጠንስ ምን ያህል መሆን አለበት? ለእነዚህ የበርካታ ሰዎች የዘውትር ጥያቄዎች የሥነ ምግብ ባለሙያ የሆኑት ጆ ልዊን ምላሽ አላቸው።
የተጠጋገኑ እና ኦሪጂናል ያልሆኑ የሞባይል ቻርጀሮች እኛንም ስልካችንንም እንደሚጎዱ ያውቃሉ?
ሊበጠስ ጫፍ የደረሰ እና የተጠጋገነ የሞባይል ቻርጅ ማድረጊያን መጠቀም ብዙዎቻችን ምንም ጉዳት የሌለው ይመስለናል። ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ ያልተጠበቀ ሲከፋም አሰቃቂ አደጋን ሊያስከትል ይችላል። በጥሩ ሁኔታ ላይ ያልሆኑ የሞባይል ቻርጀሮችን መጠቀም ምን ችግርን ሊያስከትሉ ይችላሉ? ምን ዓይነት ቻርጀሮችን ብንጠቀም ይመከራል?
ደም ግፊትን ዝቅ ማድረግን ጨምሮ ቀይ ሥር የሚሰጣቸው አምስት ጥቅሞች
የቀይ ሥርን ለየት ያለ ጠቅምን በተመለከተ የሥነ ምግብ እና የጤና ባለሙያዎች መረጃዎችን እያጋሩ ሲሆን፣ በዕለት ከዕለት ምግባችን ውስጥም ቀይ ሥርን እንድናካትት እየመከሩ ነው። ቀይ ሥር የደም ግፊትን እንዴት ሊቀንስ ይችላል? እንዴትስ ነው መመገብ ያለብን?